የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ።
መስከረም 16 ቀን 2019 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ከመስከረም 15 ቀን 2018 ዓ/ም ረፋድ ከ5:00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-
• ከ 22 ማዞሪያ ወደ መስቀል አደባባይ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች
• ከቦሌ ኤርፖርት ወደ መስቀል አደባባይ ደንበል ወይም ኦሎምፒያ ላይ እና ታች
• ከጎፋ ፣ በታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መሰቀል አደባባይ ለገሃር መብራት
• ከለገሃር ቴሌ ወደ ስታዲየም ንግድ ባንክ ክቡ ህንጻ መስቀለኛ
• ከቸርቸል ጎዳና ፣ በአምባሳደር ወደ መስቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት ላይ
• ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መስቀለኛ
• ከካዛንቺስ መብራት ወደ መስቀለኛ መቅረዝ ሆስፒታል የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል።
ነገ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.