“አዲስ አበባ ህጻናትን ለማሳደግ ምርጧ አፍሪካዊት ከተማ “ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ትምህርት ቤቶች የትውልድ ግንባታ ስራ መሰረት በመሆናቸው ቅድመ መደበኛ ትምህርትን ከማስፋፋት ጀምሮ 223 ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን፣ 5 ትምህርት ቤቶችን እና 97 ጤና ጣቢያዎችን ሞዴል በማድረግ ማሸጋገር ችለናል።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ለመማማሪያ መርሃግብር ወደ መዲናችን ለመጡ መሪዎች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉና ለህጻናት ምቹ እንዲሆኑ፣ ህጻናት በጨዋታ መልክ መማር እንዲችሉ፣ የህጻናትን ጤና ለመጠበቅ እና የተሟላ እድገት እንዲኖራቸው ትምህርት ቤቶችን እና ጤና ጣቢያዎችን ለህጻናት ምቹ ለማድረግ እና ለማሸጋገር የሰራናቸውን ስራዎች አስጎብኝተናል።
የትውልድ ግንባታ ስራችንን ውጤታማነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማረጋገጥ እነዚህን ሞዴል ስራዎች በማስፋት በቀጣይ በልዩ ትኩረት ትምህርት ቤቶች እና ጤና ጣቢያዎችን ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥለለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.