የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን አራት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ
በዚሁም፡-
አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን በከንቲባዋ የቀረቡ ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀረቡትን ሹመቶች አጽድቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.