አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት አደረጃጀት

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት አደረጃጀት

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው የመንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ፣ የከተማዋን አስተዳደር መዋቅር የሚቀይርና አዳዲስ ቢሮዎችን የሚያቋቁም ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

በዚህም መሠረት የተደረጉ መዋቅራዊ ለውጦች፦

• የሥራና ክህሎት ቢሮ፦ ለሁለት በመክፈል የሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ እና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ ተብሎ እንዲደራጅ ተደርጓል።

• ባህልና ቱሪዝም፦ የባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ እና የቱሪዝም ኮሚሽን በመዋሃድ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሆኗል።

• ትራንስፖርት፦ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ታጥፎ ተግባሩ ለትራንስፖርት ቢሮ፣ ለመንገዶች ባለሥልጣን እና ለአዲሱ ትራንስፖርት ማኔጅመንት ማዕከል ተከፋፍሏል።

• ኢንቨስትመንት፦ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አደረጃጀት ባለሥልጣን በኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተተክቷል።

• የተሰረዙ ተቋማት፦ የመሥሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የምገብ ኤጀንሲ፣ የአዲስ አበባ ሥራዎች አካዳሚ እና የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ታጥፈው ተግባራቸው ለሌሎች አካላት ተላልፏል።

• 
አዲሱ አዋጅ 7 ክፍሎች እና 98 አንቀጾች ያሉት ሲሆን፣ ቀልጣፋ አሠራር በመዘርጋት የከተማዋን ዕድገት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.