ኢሬቻ ሰላም ፣ የአንድነት ፣ የእርቅና የአብሮነት እሴቶችን የሚያጠናክር የህዝቦች የጋራ እሴት ነው
ኢሬቻ የሰላም፣ የአንድነት፣ የእርቅና የአብሮነት እሴቶችን የሚያጠናክር የህዝቦች የጋራ እሴት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እሸቱ ለማ (ዶ/ር ) ገልጸዋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የባህል ሲምፖዚየም ተካሂዷል፡፡
በመርሀ ግብሩ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እሸቱ ለማ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፣ እሬቻ የሰላም፣ የወንድማማችነት፣ የምስጋና፣ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ማጠናከሪያና የእርቅና የመሻገር ምልክት ተደርጎ፤ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ዓመቱን በናፍቆት ተጠብቆና ቀደምት የገዳ ስርዓት እሴቱን በጠበቀ መልኩ ሲከበር መቆየቱን ገልፀዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ የኢሬቻ በዓል ሰው ከፈጣሪው፣ ሰው ከሰው፣ እንዲሁም ሰው ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ሰላምና ፍቅር የሚያድስበት ታላቅ የአደባባይ በዓል ነው ሲሉ ገልፀዋል።
AMN
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.