ለመላው ሰላምና ልማት ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳንም ደስ አለን!
ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!
ለመላው ሰላምና ልማት ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳንም ደስ አለን!
የአለም የሰላም ሎሬት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልካም የሥራ ዘመን!
ዛሬ የደስታ ቀን ብቻ ሳይሆን፣ የተስፋ፣ የድልና የኢትዮጵያን ስልጣኔ የመገንባት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው!
ከብዙ ፈተናዎች በጽናት ተሻግረን፣ በጋራ ጥረታችንና በማይበገር አንድነታችን አዲስ የብልጽግና ጉዞ ጀምረናል።
ዛሬ ከሁሉም በላይ የሚጠይቀን አንድነት ነው፤ የሚጠይቀንም ሰላም ነው። ልዩነታችንን እንደ ጥንካሬ፣ አንድነታችንን እንደ ኃይል እንጠቀም። የትኛውም ልዩነት ከኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት አይበልጥም!
እጅ ለእጅ እንያያዝ፤ ልብ ለልብ እንቀራረብ፤ በሰላም እንደምር!
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሪነት፣ ለሀገራችን ሰላም፣ ሉዓላዊነት፣ ፍትሐዊነትና ሁለንተናዊ ብልጽግና በአንድነት እንቁም፤ እንተባበር፤ ተግተን እንሥራ!
ሰላም መሠረታችን ነው፤
አንድነት ጉልበታችን ነው፤
ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ናት!
ስንደመር ኃይላችን ይጨምራል፤ ስንተባበር እንቅፋቶች ይሰበራሉ፤ በአንድነት ስንቆም የኢትዮጵያ ታላቅነት ይገለጣል!
ኢትዮጵያ ትበልጽጋለች!
ኢትዮጵያ በሰላም ትጸናለች!
ኢትዮጵያ በአንድነት ታሸንፋለች! 🇪🇹
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ! ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.