አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ!
አዲስ የተሾሙት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ከቀድሞ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ከነበሩት አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል ።
በዛሬዉ ዕለት በተደረገዉ የስራ ርክክብ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረግዚኣብሔር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታሪኩ የመልካም የስራ ዘመን ምኞታቸዉን የተለዋወጡ ሲሆን፤ ቢሮዉም ለሁለቱም ተሿሚዎች መልካም የስራ እና የስኬት ዘመን እንዲሆንላቸዉ ተመኝቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.