በቅርቡ ተመርቀው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት መስጫ ተርሚናሎችን የአገልግሎት ጥቆማ
በአዲስ አበባ ከተማ ህብረተሰቡን ከፀሀይ፣ ከዝናብ፣ ከዝርፊያ በመታደግ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ዘመናዊነት ተላብሰው የትራንስፖርት ስርዓቱን ያዘመኑ የካና አራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ተርሚናሎች ለህዝብ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ።
በመሆኑም ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የካ ሾላ ተርሚናል አራት የታክሲ መስመሮች ወደ አዲሱ መገናኛ የካ ክፍለ ከተማ አጠገብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።
በዚህ መሰረት:-
1. ከመገናኛኛ---ሽሮሜዳ
2. ከመገናኛኛ---አውቶብስ ተራ
3. ከመገናኛ----ፒያሳ
4. ከመገናኛ----ስድስት ኪሎ መሆኑን እየገለፅን ሾላ ተርሚናል ውስጥ የፈረንሳይ መስመር በነበረበት ተርሚናል አገልገሎቱ እንዲቀጥል የተደረገ ሲሆን።
በተጨማሪም በአዲሱ ተርሚናል ሁለት የአውቶብስ መስመሮች 80 ቁጥር ከመገናኛ ሽሮሜዳ እንዲሁም 64 ቁጥር ከመገናኛ ፈረንሳይ ጉራራ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
በተመሳሳይ የተርሚናል ለውጥ የተደረገበት አራት ኪሎ የገበያና የመኪና ማቆሚያ ጎን የነበሩት የታክሲ መስመሮች ሙሉ በሙሉ ወደ ግንፍሌ ተርሚናል ተዛውሮ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን እያሳወቀን፤ህብረተሰቡ እነዚህን ተርሚናሎች በመጠቀም የተሳለጠና ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.