የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) የኢትዮጵያዊያን የአንድነት እና የነጻነት ምልክት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

ከጉብኝታቸው ጎን ለጎን፣ በመታሰቢያው በህንድ-አፍሪካ አጋርነት እና የወደፊት የጋራ ትብብር ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን፣ በርካታ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከዓድዋ ድል መታሰቢያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.