ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን!

እንኳን ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰላም አደረሰን!

የ2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።

ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ማንነታችን፣ የሉዓላዊነታችን አርማና የአንድነታችን ምልክት ነው። ልዩነቶቻችንን በውይይት እንፍታ፤ አንድነታችንን በመግባባት እናጠናክር፤ ሀገራችንንም በጋራ ጥረት እንገንባ!

ዛሬ ሰንደቃችንን ከፍ ስናደርግ፣ ነገ የኢትዮጵያን ክብር፣ ሰላምና ብልጽግና ከፍ ለማድረግ ቃል እንግባ!

ኢትዮጵያ በዜጎቿ አንድነት ትጠናከራለች፤ በጋራ ቁርጠኝነታችንም ለትውልድ ትጸናለች!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.