አዲስ አበባ ለሌሎች ከተሞችም ተምሳሌት ሆናለች — ዳኞች
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የእስልምና እምነት ተከታይ ዳኞች በዋና ከተማዋ የተገነቡትን የእንጦጦ ፓርክ እና የቀበና ወንዝ ዳርቻ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።
ዳኞቹ በጉብኝታቸው ወቅት እንዳመለከቱት፣ አዲስ አበባ በቅርብ ዓመታት ያስመዘገበችው ፈጣን የለውጥ ጉዞና የመሰረተ ልማት እመርታ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለጎብኚዎቿ ደግሞ ሳቢና ተመራጭ እንድትሆን አድርጓታል።
በተለይም በከተማ ውበት፣ በአረንጓዴ ልማትና በቱሪዝም መስክ የታየው ስር-ነቀል ለውጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ መድረክም እንደ ትልቅ ተምሳሌት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸው፣ የተከናወኑት ስራዎች ለሌሎች የሀገሪቱ ከተሞችም አስተማሪና አርአያነት ያለው ልምድ እንደሆነ ገልጸዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.