ከተረጅነት በመላቀቅ ራስን ለመቻል የሚደረገው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከተረጅነት በመላቀቅ ራስን ለመቻል የሚደረገው ጥረት አበረታች መሆኑ ተጠቆመ!

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ከተረጅነት በመላቀቅ ራስን ለመቻል በሚደረገው ሀገራዊ እንቅስቃሴ የከተማችንን አተገባበር የመስክ ምልከታ በማድረግ አፈፃፀሙን ገምግመዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት ተረጅነትን ለማስወገድና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማከናወን እንደ ሀገር የተቀመጠው አቅጣጫ በከተማችንም በመልካም ሁኔታ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ቋሚ የስራ ዕድሎችን በማበራከት በተረጅነት የነበሩ ዜጎችን ወደ አምራችነት የማሸጋገር ስራዎች እየተተገበሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ዶ/ር ጀማሉ በሁሉም ክ/ ከተሞች የሰብአዊ ድጋፍ ማከማቻ መጋዘኖች ተገንብተው የግብዓት ማሟላት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

የህዝባችንን የመረዳዳት እና የመደጋገፍ እሴቶችን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም ዶ/ር ጀማሉ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በመጀመሪያው የአርበኝነት ምዕራፍ የኢትዮጵያ ነፃነት ተጠብቶ መዝለቁን ጠቅሰው በሁለተኛው የአርበኝነት ምዕራፍ ደግሞ የተሟላ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ብርቱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

የሀገራችንን የኢኮኖሚ ነፃነት በማረጋገጥ ተረጅነትን ለማስወገድ እየተሰራ መሆኑን ያመላከቱት ምክትል ከንቲባው የከተማ አስተዳደሩ ተረጅነትን ለማስቆም ህዝቡን ከጎኑ በማሰለፍ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልፀዋል።

የሰብአዊ ድጋፍ ማከማቻ መጋዘን በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተገነቡ ሲሆን የጉብኝቱ ተሳታፊ ከፍተኛ አመራሮች በየካ፣ በጉለሌ ፣ በአራዳ፣ በቂርቆስ፣ በልደታ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በአቃቂ ቃሊቲ እና በቦሌ ክፍለ ከተሞች የተገነቡትን ምልከታ በማድረግ ቀሪ ስራዎች እንዲጠናቀቁ አቅጣጫ ሰጥተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.