በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላይ ያፀዱትን ቆሻ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላይ ያፀዱትን ቆሻሻ ወደ ወንዝ የጣሉ 5 የጽዳት ሰራተኞች እያንዳንዳቸው 2,000 ብር እንዲቀጡ ተደርጓል።

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በሚገኘውና ወደ አፍንጮ በር በሚወርደው የወንዝ ዳርቻ ላይ የወረዳው የጽዳት አስተዳደር ሰራተኞች የጽዳት ስራ እያከናወኑ በነበረበት ወቅት ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ያፀዱትን ቆሻሻ ወደ ወንዝ በመጣላቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደባቸው።

ድርጊቱን በፈጸሙ 5 የጽዳት ሰራተኞች ላይ እያንዳንዳቸው 2,000 (ሁለት ሺህ) ብር፣ በድምሩ 10,000 (አሥር ሺህ) ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተደርጓል።

​ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑትን የወንዝ ዳርቻዎች፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች አጠቃላይ የመሰረተ ልማት ደህንነትን ህብረተሰቡ በኃላፊነት እንዲጠብቁ መልዕክቱን አስተላልፏል።

​በከተማዋ ደንብ በሚተልፉ ማንኛውም ተቋም እና አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፆ፤ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማዎችን በነጻ የስልክ መስመር 9995 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.