የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት እና የንግድ ስርዓትን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት እና የንግድ ስርዓትን የመግራት ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝነቱ የጎላ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነት ማረጋጋት፤የንግድ ስርዓት መግራትና አዲስ አበባ ታምርት ክላስተር የቀጣይ ሶስት ወራት እቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል።

የንግድ ስርዓቱን በማዘመንና አቅርቦትን በማሻሻል የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የ90 ቀናት እቅዱን ከዳር ማድረስ ወሳኝ በመሆኑ በክላስተሩ ውስጥ የተቀናጁ ባለድርሻ አካላት በተናበበ ሁኔታ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው የክላስተሩ ሰብሳቢ ምክትል ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ አስምረውበታል። 

የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለነገ የማይባል ተግባር ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል: የኑሮ ውድነትን ማቃለል የሚቻለው ምርትን ከመጨመር ባሻገር ህጋዊ የንግድ ስርዓት ሲስፍን ነው ብለዋል::

በእቅዱ እንደተመለከተው የአዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ ለምርት አቅርቦት መሻሻል ብሎም ለኢንዱስትሪ ምርታማነት መጎልበት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል።

አቅርቦትን ከማሻሻል ጎን ለጎን ህግ የማስከበር እና ገበያን የመግራት ስራዎች ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ከቀድሞው አፈፃፀም በመነሳት አልቆ መስራት ከሁሉም የክላስተር አባለት ይጠበቃል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.