ስፖርት ለጤንነት፣ ለወዳጅነት፣ ለአንድነትና ለኢ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ስፖርት ለጤንነት፣ ለወዳጅነት፣ ለአንድነትና ለኢኮኖሚ ዕድገት!

ዛሬ 16ኛውን የአዲስ አበባ ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ እያካሄድን እንገኛለን። ስፖርት ጤናችንን ያሻሽላል፣ አንድነታችንን ያጠናክራል፣ የወዳጅነት ድልድይ ይሆናል፤ እንዲሁም ለከተማችን የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ዕድገት ዕድሎችን ይፈጥራል።

አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት እናሳትፍ። ተደራሽና ጥራት ያላቸውን የስፖርት መሠረተ ልማቶች እናስፋፋ፣ እንንከባከብ፣ በኃላፊነትም እንጠቀም።

የስፖርት ዕድገት የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። ዛሬ በስፖርት በመሳተፍ፣ ወጣቶቻችንን በመደገፍና የስፖርት መሠረተ ልማቶቻችንን በመንከባከብ የተሻለች አዲስ አበባን እንገንባ!

እናንተስ ለስፖርት ዕድገት ምን ማበርከት ትችላላችሁ? 

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.