በመዲናዋ በሚገኙ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናዋ በሚገኙ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት የስጋ አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እየቀረበ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት ጥራቱን የጠበቀ የስጋ አቅርቦት በተመጣጣኝ  ዋጋ እያገኙ መሆኑን ለኤ ኤም ኤን አስተያየታቸውን የሰጡ  ሸማቾች ተናገሩ።

በመዲናዋ የሚገኙ የህብረት ሥራ ማህበራት በሱቆቻቸው ስጋ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች እያቀረቡ ነው፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ያነጋገራቸው ሸማቾች፤ በተመጣጣኝ እና ፍትሃዊ በሆነ ዋጋ ስጋ እየሸመቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ካነጋገርናቸው ሸማቾች መካከል ግርማ ፍቃዱ፤ የደራሽ ለመርካቶ ህብረት ሥራ ማህበር ደምበኛ መሆናቸውን በመግለጽ 1 ኪሎ ስጋ በ1 ሺህ 200 ብር እየሸመቱ መሆኑን ነግረውናል።

የስጋ አቅርቦቱን በተመጣጣኝ ዋጋ  እናገኛለን፤ ሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት የኑሮ ውድነት እንዲረጋጋ የተሻለ አገልግሎት እየሰጡና ሚናቸውንም እየተወጡ ነውም ብለዋል።

ሌላኛው የህብረት ሥራ ማህበራት ደንበኛ  ዳንኤል ፋንቱ በበኩላቸው፤ የስጋ አቅርቦቱ በበቂ መጠን፣ በጥራት እና ማህበረሰቡን ባገናዘበ መልኩ በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ከደራሽ ለመርካቶ የህብረት ሥራ ማህበር አልማው ኤልያስ፤ ጥራቱን የጠበቀ በቂ የስጋ አቅርቦት እንዳለ በማንሳት ህብረተሰቡም እየገዛ መሆኑን አንስተዋል።

በሸማች ህብረት ሥራ ማህበሩ በቂ ስጋ  በማቅረብ ደንበኞች የሚፈልጉትን ሥጋ  እንዲያገኙ እየተደረገ  መሆኑን በመግለጽ፣ የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራትን አቅም ለማጎልበት እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ከቦሌ ንጋት ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበር መንገሻ አቡ፤ በሸማች ማሕበሩ በኩል በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ያለው ሥጋ ጥራቱ ተረጋግጦ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ ያለው የስጋ አቅርቦት የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና አለውም ነው ያሉት፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) በመዲናዋ በሚገኙ በተለያዩ የሸማች ማህበራት ባደረገው ምልከታ ህብተረሰቡ ከሸማቾች ማሕበራት በተመጣጣኝ ዋጋ ስጋ ሲሸምት ተመልክቷል፡፡   
AMN


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.