በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ጽ/ቤት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ ጽ/ቤት የተገነባው ማየት ለተሳናቸው ወገኖቻችን የአዳሪ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመርቆ ስለተሰጠን እጅግ በጣም እናመሰግናለን::

ይህ ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት የተጠናቀቀው ግዙፍ ፕሮጀክት ለትውልድ የሚሻገር አሻራ ሲሆን ሰው ተኮር የሆነውን የብልፅግና እሳቤያች የተተገበረበት እና ሁሌም ቃል በተግባር የሚለው መርሃችን የታየበት ለከተማችን ተጨማሪ ድምቀት የሆነ ስራ ነው::

ፕሮጀክቱ በቅርብ አስመርቀን አገልግሎት ካስጀመርነው የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ጋር ተያያዥ መሆኑ የሰው ተኮር ስራችንን እጅግ ግዙፍ ያደርገዋል።

ፕሮጀክቱን ገንብተው ላስረከቡን ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በከተማ አስተዳደሩ እና ነዋርዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::

እኛም የተረከብነውን ይህንን ፕሮጀክት ለተፈለገው አገልግሎት እንዲዉል በማድረግ በኩል አስፈላጊውን አስተዋጽኦ የምናደርግ ይሆናል ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.