የወንዝ ዳርቻ ልማት የወጣቶች የወደፊት እድልና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የወንዝ ዳርቻ ልማት የወጣቶች የወደፊት እድልና የስፖርት ቱሪዝምን የሚያበራ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስፖርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመሰጠት ዘርፉን ለማዘመንና ተደራሽነቱን በማስፋት ተጨባጭ ውጤቶች በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ምቹ ያልነበሩ ተሽከርካሪ እና እግረኛ እኩል የሚጋፋባቸው ለአደጋ የተጋለጡ በተለይም በየመንደሩ የሚኖሩ ታዳጊዎችና ወጣቶች አማራጭ ባለማግኘታቸው ኳስ ለመጫወት የተሽከርካሪን መንገድ የሚሻሙ ነበሩ። ዛሬ ይህ ታሪክ ሆኖ አልፏል ።

ከተማ አስተዳደሩ በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ዘመናዊ እና ምቹ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በመገንባት ለአገልግሎት እንዲውሉ አድርጓል። እነዚህ መሰረተ ልማቶች ነዋሪው በቅርበት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያከናውን በማስቻል የከተማዋን የስፖርት ገጽታና ቱሪዝም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ለታዳጊዎች ፣ ለወጣቶች እና ለህፃናት ምቹ ከተማን በመገንባት የከተማዋ ጎዳናዎች ለሁሉም ተስማሚ እንዲሆኑ በማድረግ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን አከናውኗል።

ዛሬ ላይ የአዲስ አበባ ውብ ጎዳናዎች ሁሉን በመልኩ አድርገው በእግረኛና በሳይክል መንገድ ተውበው ፣ በአረንጓዴ ስፍራዎች አጊጠው ለእግር ጎዞዎች እንዲሁም ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅሰቃሴዎች ምቹ ሆነዋል።አሁን ላይ በአዲስ ጎዳናዎችና በወንዝ ዳርቻ ቦታዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶች ፣ ህፃናት፣ አረጋውያን እና ጎልማሶችን መመልከት የተለመደ ባህል ሆኗል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.