አለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ለማስተናገድ ቀዳሚ መ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ለማስተናገድ ቀዳሚ መዳረሻ ከተማ አዲስ አበባ

አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና እና የዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ቀዳሚ መዳረሻ መሆኗን በተለያዩ ዘርፎች እያስመሰከረች ትገኛለች። የከተማዋ ዕምቅ ሀብትና አቅም መሰረት በማድረግ የተገነቡ በርካታ መሰረት ልማቶች ለበርካታ ታላላቅ ስብሰባዎችና ኮንፈረንሶች ተመራጭ እንድትሆን አስችሏታል።

በተለይም በከተማዋ የተገነቡ ውብ የኮሪደር ልማት የእግረኛ፣ የተሽከርካሪና የሳይክል መንገዶች፣ ንፁህ አረንጓዴ ሥፍራዎች ለዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ኮንፈረንሶች እና ጉባኤዎች ተመራጭ ከተማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ መዲናዋን ለነዋሪዎች እንዲሁም አለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ውብ እና ምቹ ትሆን ዘንድ በተከናወነው ዘርፈ ብዙ ግዙፍ የልማት ስራ በዓለም አቀፍ ጉባኤዎች አዘጋጆች ዘንድ ያላትን ተመራጭነት ከፍ እንዲል አድርጓል።

በተጨማሪም ከተማዋን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተገነባው አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ሴንተር እና አደዋ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች ትላልቅ አለም አቀፍ ስብሰባዎችና ኤግዚቢሽኖችን በኩራት ማስተናገድ የሚያስችሉ ስፍራዎች ለከተማዋ ተጨማሪ አቅም የፈጠሩ ናቸው ፡፡

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ከዋና ከተማነት በላይ የሆነች በፈጣን ለውጥ ላይ ያለች እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች መስህብ እና ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭ መዲና በመሆን እራሷን የለወጠች ከተማ ለመሆን ችላለች፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.