የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግሮችና መል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግሮችና መልዕክቶች የያዘና ከ''መስከረም እስከ መስከረም'' የተሰኘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ። መጽሃፉ ላይም ሙያዊ ውይይት በወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።

በመደረኩም ተማሪዎች ከመጽህፉ የተመረጡ ገጾችን ለውይይት መነሻ ሃሳብ እንዲሆኑ በንባብ ያቀረቡ ሲሆን፣ በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ተሳታፊዎችም በመጽሃፉ የተሰነዱ መልዕክቶች ላይ ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መጽሃፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ አገር አቀፍ ሁነቶች፣ ዓለም አቀፉ ጉባኤዎችና በዓላት ላይ ያስተላለፏቸውን 91 መልክቶችና ንግግሮች ያያዘ ነው።

#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.