ለሸማቹ ህብረተሰባችን የቀረቡ 282 የሰንበት ገበያዎች በአዲስ አበባ
ባለፉት አምስት ዓመታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና በሰው ህይወት ላይ ተጨባጭ ለዉጥ ያመጡ በርካታ ሰዉ ተኮር ተግባራትን በማከናወን የከተማዋን ሁለተናዊ እድገት ማረጋገጥ ተችሏል ።
ከተማን ማልማት ከመሰረት ልማት እድገት ባሻገር ሰዉ ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት ላይ መስራት መሆኑን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናችን አዲስ አበባ የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቅለልና ገበያውን ለማረጋጋት በአምስቱም የከተማዋ መግቢያ በሮች አጅግ ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት በመገንባት በሸማቹ ማህበረሰብ ዘንድ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ተችሏል።
በተለይም መንግስት የህብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ከ282 በላይ የሰንበት ገበያዎች ለነዋሪው ቅርብ በሆኑ አካባቢዎችና በሁሉም ክፍለ ከተሞች በማስፋፋት እንዲሁም የበጀት ድጎማ በማድረግ መሰረታዊ ሸማች የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀትና በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ በከተማዋ ጥራት ያለዉ ምርት በስፋት እንዲቀርብ እና የዋጋ መረጋጋት እንዲሰፍን ማድረግ ችሏል፡፡
በነዚህ የገበያ ማዕከላት ምርት እና ምርታማነትን በመጨመር ፣ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ፣የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር እና የደላሎችን ሰንሰለት በመበጣጠስ እንዲሁም በኬላዎች የሚስተዋለዉን ያልተገባ ክፍያን በመስቆም በሻጭና በሸማች መካከል ቀጥታ ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ ተችሏል፡፡
በአጠቃላይ እነዚህ በመዲናችን የተገነቡ ዘመናዊ የገበያ ማእከላትና የቅዳሜና ዕሁድ ገበያዎች አዲስ አበባን ከአጎራባች ከተሞች ጋር በማስተሳሰር የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት ዉጤቶች በተመጣጣኝ እና የሸማቹን ኪስ በማይጎዳ መልኩ በስፋት እና በጥራት በማቅረብ ፣አርሶ አደሩን ጨምሮ የከተማዋ ሸማችና አምራች ቀጥታ በማገናኘት ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት በማስፈን ሁለተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የለዉጡ ትሩፋቶች መሆናቸው ማሳያ ናቸው ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.