በCOP31 በአንታሊያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የአ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በCOP31 በአንታሊያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ የአየር ንብረት ለውጥ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አንቶኒ ኦኮን ንዮንግ እና የGlobal Covenant of Mayors አምባሳደር እና የፓሪስ ቀድሞ ከንቲባ አን ሂዳልጎ ጋር ተገናኝተን በአዲስ አበባ የአየር ንብረትና ዘላቂ የከተማ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል።

በተለይም የአየር ንብረት ፋይናንስን በቀጥታ ለከተሞች ማድረስ፣ የፕሮጀክት ዝግጅትና አፈጻጸም አቅምን ማጠናከር፣ እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት፣ በወንዝ ዳርቻ ልማት፣ በከተማ መልሶ ማልማትና በከተማ ግብርና የተገኙ ልምዶችን ለመማማርና ለመለዋወጥ የሚያስችሉ የትብብር መስኮችን ለማጠናከር ተስማምተናል።

አዲስ አበባ የCOP32 አስተናጋጅ ከተማ በመሆኗ፣ የአፍሪካ ከተሞችን የጋራ የአየር ንብረት ቅድሚያዎች፣ የፋይናንስ ፍላጎቶችና የልማት አጀንዳ በአንድ ድምፅ ለዓለም ማቅረብ የሚያስችል መድረክ ለመፍጠር ትልቅ እድል አላት።

የጋራ ድምፃችንን በማጠናከር፣ የአፍሪካ ከተሞችን የልማት ፍላጎት፣ የፋይናንስ ተደራሽነትና የቴክኖሎጂ ትብብር እናሳድጋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.