ባለፈው ዓመት 'የመደመር ትውልድ' መፅሃፍን በመረቅንበት ወቅት በኦሮምያ ክልል የሚሸጡ መጽሐፎች ገቢውን የሶፍ ኡመር አካባቢን ለማልማት እንዲውል አበርክተን ነበር።
ዛሬ ስራው የደረሰበትን አስደናቂ ርምጃ ተመልክተናል። ባሌ ካለው ሰፊ የታሪክ ሃብት እና የተፈጥሮ ስጦታ አንፃር እምቅ ሀብት ያለበት አካባቢ ነው። ድንቅ መስህብ ያላቸው መልክዓ ምድሮች ከመሰረተ ልማት እና የመገናኛ ማሳለጫዎች መሻሻል ጋር ለአካባቢው የበለጠ እድገት ሊያስገኙ ይችላሉ። በአቅራቢያ የሚገኘው የዲንሾ ፓርክ የአካባቢውን ሳቢነት የበለጠ የሚጨምር ነው።
የሶፍ ኡመር ፕሮጀክት አመርቂ አጀማመር የጠንካራ ፕሮጀክት አመራርን ጠቀሜታ የሚያጎላ ሲሆን የስራው ሂደት ባለበት ደረጃ እንኳ ሰፊ የስራ እድል የፈጠረ የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃም በእጅጉ የሚያሻሻል ይሆናል።
የጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.