አዲስ አበባ፡ ከዲፕሎማሲ ማዕከልነት እስከ ማራኪ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ፡ ከዲፕሎማሲ ማዕከልነት እስከ ማራኪ የቱሪዝምና የከተማ ልማት መዳረሻነት!

በአፍሪካ ሴሌብሪቲስ 2026 ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ወደ መዲናችን አዲስ አበባ የመጡ እንግዶች፣ የአዲስ አበባን አዲስ ገጽታና ከተማዋ በፈጣን የለውጥ ግስጋሴ እያስመዘገበች ያለውን አስደናቂ የልማት ስራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። 

ይህ ጉብኝት አዲስ አበባ የአፍሪካ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ማዕከል ከመሆኗም ባሻገር፣ የዘመናዊ ከተማ ልማት፣ የባህል እና የቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ መሆኗን እንግዶቹ በተግባር ያዩበት አስደናቂ አጋጣሚ ተመላክቷል።

እንግዶቹ ጉዟቸውን የጀመሩት የሀገር በቀል እውቀትና የባህል ምግባችን መገለጫ ከሆነው የጉለሌ እንጀራ ማእከል ነው። ይህ ማእከል ለበርካታ ሴቶች ሰፊ የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ የኢትዮጵያን የባህል ምግብ ዝግጅትና እሴት ለአህጉሪቱ እንግዶች በሚገባ ያስተዋወቀ የልማት ተቋም መሆኑን በጉብኝታቸው ማረጋገጥ ችለዋል።

በመቀጠል የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምንና የከተማዋን ገፅታ ሙሉ ለሙሉ እየቀየሩ የሚገኙትን የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያመጡትን ስነ-ምህዳራዊ ለውጥ፣ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች መስፋፋት እንዲሁም ለነዋሪዎች የፈጠሩትን ምቹ የኑሮና የኢኮኖሚ እድል በአድናቆት ገልጸዋል።

በተለይም አዲስ አበባ የከተማ ልማትን ከስራ እድል ፈጠራ፣ ከባህል፣ ከቅርስ፣ ጥበቃና ከቱሪዝም መስህብነት ጋር በአስደናቂ ሁኔታ አቀናጅታ እየሰራችው ያለው ስራ ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞችም ትልቅ ልምድ የሚሰጥ መሆኑን ጎብኚዎቹ መስክረዋል። አዲስ አበባችን ዛሬም እንደ ስሟ አዲስ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም ለእንግዶቿ ማራኪ ሆና አለምን በኩራት እያስተናገደች ትገኛለች።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.