መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
በመርካቶ የበጎነት መንደር/በቅጠል ተራ የተገነቡት ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች ከተራ የግንባታ ሥራ በላይ፣ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚቀይሩ፣ የቤተሰቦችን ተስፋ የሚያድሱና የማህበራዊ ፍትህን በተግባር የሚያረጋግጡ የመደመር መንግሥት ቁርጠኝነት ማሳያዎች ናቸው።
የቤት ችግርን መቅረፍ ማለት የአንድን ቤተሰብ ነገ መገንባት፣ የልጆችን የተሻለ ዕድል ማረጋገጥ፣ የኑሮ ደህንነትን ማጠናከርና የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ማነቃቃት ነው።
በመሆኑም ይህ ልማት ከአንድ ቤት ባለቤት መፍጠር በላይ የሚሄድ ማህበራዊ እሴት አለው።
ዜጎች በተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ፣ ቤተሰቦች በኢኮኖሚያዊ ጫና ሳይገደቡ የወደፊት ዕቅዳቸውን እንዲያሳኩ፣ ማህበረሰቡም በመተሳሰብና በአንድነት እንዲጠናከር የሚያግዝ ተጨባጭ ለውጥ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመደመር መንግሥት የከተማ ልማት ትግበራ ጋር በመዋሃድ፣ የዜጎችን ፍላጎት የመመለስ ቁርጠኝነቱን በተግባር እያሳየ ነው።
ቃልን በተግባር እያረጋገጠ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ኑሮና አኗኗር ለማሻሻል በ24/7 በልዩ ትኩረት እየሰራም ይገኛል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.