አዲስ አበባ በአካታች የከተማ ልማት ስራዎች ያላ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ በአካታች የከተማ ልማት ስራዎች ያላትን ተሞክሮ ለጀርመኗ እህት ከተማ ላይፕዚሽ ያጋራችበት የልምድ ልውውጥ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካቶ ትግብራ ስራዎች ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በልማት፣ በትምህርትና በስራ እድል ፈጠራ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ ስማርት ሲቲ ከተማን ለመግንባት በምታደርገው ጥረት የአካቶ ትግበራ ስራዎች ሴቶችን፣ ህጻናትን፣ወጣቶችን እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች መሰራታቸውን ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ እና የጀርመኗ ላይፕዚሽ የሁለትዮሽ እህትማማች ከተሞች ግንኙነት ለአመታት የዘለቀ ሲሆን በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ የልምድ ልውውጥ እየተደረገ የጋራ የከተማ ልማት እሴቶች ላይ አብሮ የመስራት ልምድ እየተቀመረ ይገኛል።

ከ5 አመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ባዩት ለውጥና በተሰሩ ስራዎች መደነቃቸውን ከጀርመኗ እህት ከተማዋ ላይፕዚሽ የመጡ የልዑካን ቡድን ገልጸዋል፡፡ 

በቆይታቸው የሚቀመሩ ተሞክሮዎች በከተማቸው ለተለያዩ ስራዎች በግብአትነት እንደሚያግዛቸውም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል የላይፕዚሽን አካቶ ባህል ትምህርት ዳሬክተር ጃና ዘህለ እንደገለጹት፡- በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎች በተለይም በህጻናት መዝናኛ የተሰራው የአካቶ ትግበራ ስራ ደስ የሚል ስሜትን የሚፈጥር እና በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ከጀርመኗ እህት ከተማዋ ላይፕዚሽን ጋር እየተካሄደ የሚገኘው የአካቶ ትግበራ የልምድ ልውውጥ መድረክ በተለያዩ መርሃ ግብሮችና በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ የአካቶ ትግበራ ስራዎችን በመጎብኘት ከዛሬ ህዳር 7/2019 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ለ5 ቀናት እየተካሄደ ይቆያል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.