አዲስ አበባ በአካታች የልማት ሥራዎች ዙሪያ ለጀ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ በአካታች የልማት ሥራዎች ዙሪያ ለጀርመኗ ላይፕዚሽ ከተማ ልምዷን እያጋራች ነው

​አዲስ አበባ ከተማ በመዲናዋ የተከናወኑ አካታች የመሠረተ ልማት ሥራዎችን አስመልክቶ ለእህት ከተማዋ፣ ለጀርመኗ ላይፕዚሽ ልዑካን ልምዷን በማጋራት ላይ ትገኛለች።

​የልምድ ልውውጥ ሁለቱ ከተሞች በቀጣይ በሚያከናውኗቸው የጋራ ፕሮጀክቶች ዙሪያ የላቀ ትብብር ለመመሥረት የሚያስችል ነዉ ።
ልዑካኑ በቆይታቸው የበሻሌ የወንዝ ዳርቻ ፓርክ፣ የጎሮ ጫካ ፓርክ፣ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን «አዲስ መንደር» እንዲሁም በከተማዋ የሚገኙ ሕዝባዊ መገልገያዎችን እና በመከናወን ላይ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየተዘዋወሩ እየጎበኙ ይገኛሉ። በጉብኝታቸውም ለሕፃናት፣ ለሴቶች፣ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች ምቹና በእኩልነት ተደራሽ የሆኑ ፓርኮችንና ሕዝባዊ ቦታዎችን ጨምሮ ከቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት አገራዊ ተሞክሮ ልምድ ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

​በልምድ ልውውጡ ወቅት የላይፕዚሽ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት የስራ ሀላፊዎች፣ የከተማዋ ፕላንና ልማት ጽሕፈት ቤት ከፍተኛ ሙያተኞች እንዲሁም በአካታች የከተማ ልማትና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዙሪያ የሚሠሩ የተለያዩ አካላት የተገኙ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ከተማም አቻ የሴክተር መሥሪያ ቤቶች ተሳትፈዋል።

​ለልምድ ልውውጥ ከጀርመኗ ላይፕዚሽ ከተማ የመጡት ልዑካን በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እስከ መጪው ዓርብ ድረስ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.