ሰርክ አዲስ ብስራት የሚሰማባት አዲስ አበባ ዛሬ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሰርክ አዲስ ብስራት የሚሰማባት አዲስ አበባ ዛሬም በሌላ ስኬት በሌላ አዲስ የድል ታሪክ ብቅ ብላለች። ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገን ይሁን!

ሰርክ አዲስ ብስራት የሚሰማባት አዲስ አበባ ዛሬም  በሌላ ስኬት በሌላ አዲስ የድል ታሪክ ብቅ ብላለች።

ለከተማዋ ሌላ ተጨማሪ ከፍታና  የውበት መጎናፀፊያ የሚያላብስ፤  ውብ ገፅታ ብቻ ሳይሆን ምቾት የተላበሰ ዘመናዊ  ሁለንተናዊ  ግልጋሎት  የሚሰጥ የቦሌ የኮሪደር ልማት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በተገኙበት አስመርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል ፡፡

በዚህ ዘመናዊ ግዙፍ  የኮሪደር ልማት  የተለያዩ የቦሌ አካባቢዎች የለሙ ሲሆን እነዚህም፦

• ከቦሌ መድኃኒዓለም – ጎላጉል – እስከ እንግሊዝ ኢምባሲ
• ከቦሌ መድኃኒዓለም – እስከ ሞኤንኮ
• ከቦሌ ትምህርት ቤት – እስከ አደይ አበባ ሞዴል መንደር
• ከኢምፔሪያል ሆቴል – እስከ ሻላ መናፈሻ
• ከቺቺኒያ – እስከ ቦሌ ሩዋንዳ
• ከአደይ አበባ ስታዲየም – እስከ ቦሌ መንገድ
• የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ኔትወርክ

 አጠቃላይ የልማት ስፋትና መሠረተ ልማት ሰራዎቸ
• 57 ሄክታር የልማት ቦታ
• 17 ኪ.ሜ. የመንገድ ርዝመት
• 34.ኪ.ሜ. የእግረኛ መንገድ
• 8 ኪ.ሜ. የሳይክል መንገድ
• 3 የተሽከርካሪና የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች
• 5,880 መኪናዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚችሉ የመኪና ማቆሚያዎች
• 150 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮች
• 13 የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች

 የመሬት ውስጥ መሠረተ ልማት ሰራዎቸ
• 17 ኪ.ሜ. የፍሳሽና የጎርፍ ማስወገጃ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የመጠጥ ውሃ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የኤሌክትሪክ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የቴሌኮም መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የITS መስመሮች

የንግድ፣ የሥራ፣ የመኖሪያና የመዝናኛ ልማት ሰራዎቸ
• 91 የንግድ ሕንፃዎች
• 3,116 የንግድ ሱቆች
• 152 ቤቶችን የያዘ ሞዴል መንደር
• 33 ካፍቴሪያዎች
• 20 ሬስቶራንቶች
• 440 የታደሱ ሕንፃዎች
• 2 ቤተመጻሕፍት
• 7 የልጆች መጫወቻዎች
• 7 የስፖርት ሜዳዎችና ጂምናዚየሞች
• 7 ፏፏቴዎችና ፋውንቴኖች
• 5 የህዝብ መዝናኛና ፕላዛዎች
• ሰፊ አረንጓዴ ቦታዎች
• የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች

የተቋማት ልማት ሰራዎቸ
• 2 የትምህርት ቤት ግንባታና ማስፋፊያ ሕንፃዎች
• 2 የፖሊስ ጣቢያ ግንባታና ማስፋፊያ ሕንፃዎች
• 1 የቱሪስት መረጃ ማእከል

በአጠቃላይ በግንባታ ወቅት 23,000 ዜጎች የሥራ ዕድል ያገኙ ሲሆን በቀጣይም ለ10 ሺ ሰዎች ቋሚ የሥራ ዕድሎች ይፈጠራሉ። ለዚህ ፕሮጀክት ታሪካዊ አሻራችሁን ያኖራችሁ ፤ በታለመለት ጊዜ መጠናቀቅ ሌት ተቀን የላፋችሁ የደገፋችሁ እና ያስተባበራችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች ፤ የስራ ተቋራጮችና ባለሙያዎች እና የአካባቢው ማህበረሰብ  በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም መላውን ህዝብ አደራ ለማለት የምፈልገው፤ ይህንን የልማት ሥራ፣ ይህንን ውበትና አሻራ እንዲሁም ሀብትና ንብረት በባለቤትነት ስሜት ተንከባክቦ በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ እንዲያደርግ ነው።

ስንተባበር እንችላለን፤ በጋራ ስንሆን እናሸንፋለን! 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.