በአዲስ አበባ እና በጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ መካከል ሲካሄድ የነበረው ሁሉን አካታች የከተማ ልማት የልምድ ልውውጥ ተጠናቀቀ።
በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታሪኩ በሰጡት ማብራሪያ፡- አዲስ አባባ በሙያ ስልጠና ኮሌጆች እና በከተማ ፕላን ዘርፎች ሁሉን አካታች የከተማ ልማት ስራዎች መሰራታቸውን ግልፀዋል፡፡
በተለይም በወንዝ ዳርቻ ልማት፣ በትምህርት ቤቶች ስልጠና፣በህንጻ ግንባታና በመዝናኛ ቦታዎች የተሰሩ የልማት ስራዎች አካል ጉዳተኞችን፣ህጻናትንና ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው፡፡
ይህ የልምድ ልውውጥ መድረክም በቀጣይ አብሮ ለመስራትና ሁሉንም የህብረትሰብ ክፍሎች በትምህርት፣ በሙያ ስልጠና በከተማ ልማት ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው አቶ ሙሉቀን ታሪኩ ተናግረዋል፡፡
የላይፕዚግ ከተማ የማህበራዊ ተሳትፎ እና አካታችነት አስተባባሪ ወ/ሮ አኔግሬት ፕሪጌ በበኩላቸው የናኮፓ አካታች ፕሮጀክት እህትማማች ከተሞች በሆኑት ላይፕዚግ እና አዲስ አበባ መካከል የተጀመረ የትብብር ፕሮጀክት አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎና ተጠቀሚነት ያሳደገ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች በሙያና ስልጠና ኮሌጆች እና በከተማ ፕላን ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በአጭር ጊዜ የተሰራው ስራ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል።
ከተማዋ ውስጥ የሕፃናት መዝናኛዎችና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መገንባታቸውን የተመለከቱት ወ/ሮ አኔግሬት ፕሪጌ ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ በተለይ በህጻናት መጫዎቻና ማቆያ ዴይ ኬር ያገኘትን ልምድ በሙያቸው ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም አዲስ አበባ ከተማ በአካታች የከተማ ልማት ስራዎች የተሰሩ የልማት ስራዎች ለሌሎች ሃገራትም ልምድ የሚወሰድበት ስራ መሆኑ በመድረኩ ተገልጻል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.