5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) ጎን ለጎን ውይይት አድርገናል::ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

በCPHIA 2026 ጉባኤ ወቅት ከሴራሊዮን ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ማዳ ቢዮ ጋር በመገናኘት የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅም ዙሪያ ትብብራችንን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

በCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከቡሩንዲ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስት ንዳይሺሚዬ ጋር ውይይት አድርገናል። በቅርብ ጊዜ ያደረግናቸውን ምክክሮች መሠረት በማድረግ፣ ይህ ውይይት የጋራ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ጉዳዮች ለመዳሰስ፣ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማስፋት እንዲሁም የጋራ ቀጣናዊ እና አህጉራዊ አጀንዳዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ተግባራት ለመለወጥ የሚያስችሉ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ ዕድል ሰጥቶና

በCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ጋር ውይይት አድርገናል። በውይይታችንም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ እና ለዘመናት የቆየ ግንኙነት በድጋሚ ያረጋገጥን ሲሆን፣ ተግባራዊ ትብብርን እና ተጨባጭ ውጤቶችን በማምጣት አጋርነታችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረናል።

በCPHIA 2026 ጉባኤ ጎን ለጎን ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ስብሰባ አድርገናል። ውይይታችን ታሪካዊ ግንኙነታችንን ወደ ላቀ የሁለትዮሽ ትብብር እና የጋራ ቀጣናዊ እድገት መለወጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.