"ሀገር የምትገነባው ዛሬ በምንሰራ እና በምናኖረ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ሀገር የምትገነባው ዛሬ በምንሰራ እና በምናኖረው ተሻጋሪ ስራ ነው።" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ያሰለጠናቸውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን በዛሬው እለት አስመርቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምርቃት መርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ መንግስት በትምህርት ተደራሽነት ላይ ያስመዘገበውን ስኬት በትምህርት ጥራት ረገድም በመድገም በአጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱ ያጋጠሙንን ስብራቶች ለመጠገን ጥራት ላይ አተኩሮ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ከንቲባ አዳነች አክለውም ሀገር የምትገነባው ዛሬ በምንሰራው እና በምናኖረው ተሻጋሪ ስራ ነው ያሉ ሲሆን ተመራቂ መምህራኖች ዛሬ የምትዘሩት የእቀት ዘር የሀገር ፍቅር ያለው፣ በፍቅር የታነፀ፣ ውጤታማ የሚሆን እና ማህበራዊ መስተጋብሩ የጠነከረ ትውልድ እንዲኖረን ያስችላል እና በፍፁሜ ሀላፊነት እንድትሰሩ አደራ ልላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮግራምን ቀርፆ ውጤታማ በማድረግ አዲስ አበባን ለህጻናት እድገት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በአፍሪካ ከሚገኙ ከተሞች ግንባር ቀደም ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የገልፁት ከንቲባ አዳነች፣ የዛሬ ተመራቂ መምህራን የሚያስተምሩዋቸው ህጻናት ቀጣይ የትምህርት ጉዟቸው ውጤታማ እንዲሆን መሰረት የሚጥሉ እንደመሆናቸው ኃላፊነታቸውን በዕውቀትና በከፍተኛ ተነሳሽነት በመወጣት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚጠበቅባቸው የአደራ መልክት አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ጨወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ-ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ ህጻናት አካላዊ እና አእምሯዊ እድገታቸው እንዲጎለብት ከማስቻላቸው ባሻገር ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት የሚያዘጋጁ በመሆናለው የዛሬው መርሀ ግብር ትምህርቱን በሰለጠነ የሰው ሀይል እና ለደረጃው ብቁ በሆኑ መምህራንን እንዲመራ ለማስቻል አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ለበለጠ መረጃ

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.