በውቧ የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በውቧ የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ዲፕሎማቶች፥ የአፍሪካ ህብረት (AU) ሠራተኞች፣ እና የከተማችን ነዋሪዎች በጋራ የተሳተፉበት ደማቅ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሂደ።

ይህ ሁነት የአፍሪካዊ አንድነት፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ እንዲሁም የከተማችንን የሰላምና የዲፕሎማሲ ማዕከልነት የሚያረጋገጥ ነው።

አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ መጠን፣ የአህጉራችንን ህዝቦች የሚያቀራርቡ እና የወንድማማችነትና እህትማማችነት ትስስርን የሚያጠናክሩ እንዲህ ያሉ ሁነቶችን ተጠናክረው ቀጥለዋል።

ውድድሩ የከተማችንን የአብሮነት፣ የሰላምና የዲፕሎማሲ መንፈስ በጉልህ የተንፀባረቀበት ልዩ ሁነት ነው።

በከተማችን እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትና የከተማ ማስዋብ ሥራዎች፤ ለነዋሪዎችም ሆነ በከተማችን ለሚኖሩ ዲፕሎማቶች ምቹ፣ ጽዱ እና ለጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ተስማሚ መዲናን መፍጠራቸውን በተግባር የታየበት ነው። 

አዲስ አበባን ይበልጥ ውብ፣ ሰላማዊ እና ለሁሉም ምቹ የማድረግ ጉዟችን ተጠናክሮ ቀጥሏል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.