የዘንድሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራችንን ለአቅመ ደካሞችና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች ሶስት ባለ 9 ወለል ህንጻዎችን ልደታ ክፍለ ከተማ ላይ ወደ ግንባታ በማስገባት ጀምረናል።
በክረምት የቤት ግንባታ እና እድሳት ስራችን 3500 ቤቶችን በመገንባት 17 ሺሕ 500 አቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተስብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ሲሆን፣ በባለፈው የክረምት እና የበጋ የበጎ ፈቃድ ስራችን 6730 ቤቶችን በመገንባት ለነዋሪዎች ማስተላለፍ ችለናል። ካላቸው በማካፈል በዚህ ስራ ላይ የተሳተፉ አካላትን ሁሉ በነዋሪዎቹ ስም በድጋሚ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ዛሬ ያስጀመርናቸውን ሶስት ባለ 9 ወለል ህንጻዎች ከቲኤንቲ ኮንስትራክሽን፣ ኢትዮ ኮቴጅ እና ከአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር የምንገነባ ሲሆን የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቅለል በጀመርነው ስራ ላይ በመሳተፍ ከጎናችን ስለቆሙ በነዋሪዎቻችን ስም አመሰግናቸዋለሁ።
በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብራችን 15 ዋና ዋና ፕሮግራሞችን እና 18 መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የምናደርግ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.