አዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ግንቦት 24 ፣ 2016...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ግንቦት 24 ፣ 2016 በ3ኛ አመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የመካከለኛ ዘመን የ2017 በጀት ጣሪያ ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል ።

ካቢኔው ዛሬ ባደረገው ከ2007 - 2019 በጀት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የወጪ ማዕቀፍ ውይይት መሰረት የ2017 በጀት ዓመት ከተለያዩ የገቢ አርዕስቶች 230.39 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ያቀደ ሲሆን የበጀት ድልድሉም ከጠቅላላ በጀት ውስጥ 61% ለካፒታል ወጪ ሆኖ በጀቱም በዋናነት በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ የትራንስፎርሜቲቭ ፕላን ዝግጀት ለተያዙ ቁልፍና እድገት ተኮር ዘርፎች የበጀት ድልድሉ የትኩረት አቅጣጯ መሆን አንዳለበት ካቢኔው ተወያይቷል።

በመጨረሻም አዲስ አበባ በገቢ ግብር በጀቷን የምታስተዳድር ከተማ እንደ መሆኗ መጠን የገቢ አቅሟን አሟጦ መሰበሰብ የሚገባ መሆኑ አጽንኦት ሰጥቶ በመወያየት የገቢ አሰባሰብ ስርአት ላይ ትኩረት ሰጥተው ተቋማት መስራት የሚችሉበት ቀጣይ አቅጣጫም በትኩረት ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግበት ውሳኔ አሳልፏል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.