ለዘመናት ልዩነቶችን በሃይልና በጠመንጃ ከመፍታት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለዘመናት ልዩነቶችን በሃይልና በጠመንጃ ከመፍታት ታሪክ በመውጣት በሰለጠነ መንገድ በውይይት ለመፍታት የሚያግዘን በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ሃገራዊ ምክክር በርዕሰ መዲናችን አዲስ አበባ መጀመሩ ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ነው።

ሃገራዊ ምክክሩ እንደ ሃገር ያሉንን በርካታ መልካም ነገሮቻችንን በሚያጠለሽ መልኩ መጥፎ ገፅታችን ከነበረው ልዩነቶችን በጠመንጃ እና በጉልበት ከመፍታት እና የአንድ ሃገር ህዝቦች በዚህ ልክ በጠላትነት ከመፈራረጅ ተላቅቀን በውይይት ብቻ በመፍታት በሃገራችን ዘላቂ ሰላም በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

ይህ ለሃገራችን ተጨማሪ ታሪክና ታላቅ ውጤት የሚያስገኘው ሃገራዊ ምክክር፣ ህዝባችን የስልጣን እና የጉዳዩ ባለቤት በመሆን ራሱ በቀጥታና በመረጣቸው ተወካዮቹ አማካኝነት አጀንዳዎችን አቀራራቢ በሆነ መንገድ በምክክር በመፍታት ሃገራዊ መፍትሄ እንደሚያመጣ ይጠበቃል።

ስለዚህ ውድ የከተማችን ነዋሪዎች በተለይም ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተወክላችሁ በምክክር መድረኩ ላይ በመሳተፍ ላይ የምትገኙ ሁሉ፣ ይህ ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነት በመሆኑ ከማንኛውም የግልና የቡድን ስሜት እና አመለካከት በመውጣት በብቃት በመሳተፍ የልዩነት መፍቻ መንገድ ውይይት ብቻ መሆኑን በማሳየት አዲስ ታሪክ በመስራት ፋና ወጊ ሚናችሁን እንደምትወጡ ትልቅ ተስፋ አለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.