በመኖሪያ ቤት አከራይ እና ተከራይ መካከል ያለው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመኖሪያ ቤት አከራይ እና ተከራይ መካከል ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት አዋጁን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ

የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 እና መመሪያ ለመተግበር እንዲያስችል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

አቶ ሞገስ ባልቻ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ የውይይት መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት መንግስት የቤት ጥያቄን ችግር ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማካሄዱን ጠቅሰው በመኖሪያ ቤት አከራይ እና ተከራይ ያልተገራ የዋጋ ግመታ መግራት እና የአከራይ ተከራይ መሀል ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አዋጁን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ክብርት ቅድስት ወልደጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እዳሉት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር የተረጋጋ ፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሁም የአከራይ እና የተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለመፈፀም አዋጁ መደንገጉን ገልፀው አዋጁ እና መመሪያውም ከሰኔ አንድ ጀምሮ ተግባራዋ ይሆናል ብለዋል።

አዋጁን አቶ ፀጋዬ ሞሼ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤት ልማት ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ ያቀረቡ ሲሆን መመሪያውን ደሞ አቶ አሰፋ መብራቴ የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሁሉም ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፣ ፖርቲ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.