ሚድሮክ ኢንቨስትመን ግሩፕ በ128 ሚሊየን ብር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሚድሮክ ኢንቨስትመን ግሩፕ በ128 ሚሊየን ብር ለኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚውሉ ማሽኖችና የህክምና ግብዓቶችን ለመግዛት ስምምነት ፈፀሙ ።

ስምምነቱ የተፈጸመው ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮና ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ተቋማት ነው።

የድጋፍ ስምምነቱን የፈረሙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ በመረሀ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት :-አሁን በሚዲሮክ ኢንቨስትመንት በኩል እየተደረገ ያለው ድጋፋ የ180 ታካሚዎችን የህክምና ግብዓት ለሶስት ዓመታት የሚሸፍን ይሆናል ብለዋል ።

 

ከተማ አስተዳደሩ አስቀድሞ ከበጀቱ ቀንሶ በነጻ ሲሰጥ የነበረውን የኩላሊት ህክምና አገልግሎት የሚያጠናክርና አቅም የሚፈጥር ጭምር መሆኑን ኃላፊው ዶ/ር ዮሃንስ አስታውቋል።

የተፈጸመው ስምምነቱ ከዚህ ቀደም ከተማ አስተዳደሩ በዳግማዊ ሚኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል ሲሰጥ የነበረውን የኩላሊት እጥበት ህክምና በዘላቂነት ለማጠናከር የሚያስችል ነውም ተብሏል።

በፊርማው ወቅት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው አገልግሎቶች አንዱ ለተቸገሩት መድረስ ነው ያሉት የድርጅቱ ተወካዩ አምባሳደር አሊ ሱሌማን ከዚህ ቀደም ለስድስት ወር አገልግሎት የሚሰጡ 10 ማሽኖችና ግብዓቶችን ገዝተናልም ብለዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በተጨባጭ ከመወጣት ረገድ ለ180 ታካሚዎች ለሶስት አመታት የሚያገለግሉ ማሽኖችና የህክምና ግብዓቶችን ለመግዛት ዝግጁነቱን ማጠናቀቁን ተወካዩ አረጋግጠዋል ።

በድርጅቱ በኩል ከዚህ ቀደም በተመሣሣይ 10 ማሽኖችና ተጓዳኝ ግብዓቶችን ለማሟላት የተደረገው ድጋፍ ከ128 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የጠየቀ መሆኑም በፊርማው ወቅት ተጠቁሟል ።

በ128 ሚሊየን ብር ወጪ የሚደረግባቸው ማሽኖችና ግብዓቶችን በአጭር ጊዜ ለመግዛት አስፈላጊው ርብርብ እንደሚደረግ የተናገሩት ደግሞ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ናቸው።

መሰል ማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ተግባራት ላይ ሌሎችም ሊሳተፉበት እንደሚገባ በስምምነቱ ወቅት ጥሪ ተደርጓል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.