በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር መኩሪያ መርሻዬ የተመራ ልዑክ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
የኮሪደር ልማት ስራውን ሂደት በተመለከተ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ጥራቱ በየነ የልዑክ ቡድኑን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ገለፃ አድርገዋል።
ክቡር ጥራቱ በየነ ለልዑካን ቡድኑ ባደረጉት ገለፃ የኮሪደር ልማት ስራው የከተማዋን መሰረተ ልማት በማሻሻል የአረንጓዴ ልማት ስራን እና ህዝባዊ የመዝናኛ ስፍራን አካቶ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን አብራርተው በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ 24/7 የስራ ባህልን አለማምዷል ብለዋል።
የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር መኩሪያ መርሻዬ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለው ስራ መነሳሳትን የፈጠረ መሆኑን በመግለፅ የሐዋሳ ከተማ ለጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ የልማት ስራውን ለማፋጠን እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
ልዑኩ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.