የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ/ም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ስኬታማ በማደረግ የህዝባችንን የመረዳዳትና የመደጋገፍ እሴት ከፍ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በዕቅዱ ላይ መክረዋል::

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ሀላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ዓመቱን ሙሉ ለማከናወን ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልፀው ከተማችን በበጎ ስራዎቿ በአገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሞክሮ የሚቀሰምባት መሆን መጀመሯን አመላክተዋል።

በየደረጃው የሚገኘው አመራር የተደራጀ አመራር በመስጠቱ እና የህዝባችን ተሳታፊነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ በማደጉ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገለፁት አቶ አለማየሁ በቀጣይም በጥበቃ ዲሲፕሊን በመምራት ለህዝባችን ኑሮ መሻሻል ያለውን አቅም መጠቀም እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይመር ከበደ በበኩላቸው ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተከናወኑ ያሉ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት ከዘላቂ ዕድገት እና ከከተማ ዕድገት ጋርም የተጣጣሙ መሆናቸውን በመጠቆም በብዛትም በጥራትም ከፍ በማድረግ ለአዲስ አበባ ማርሽ ቀያሪ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ/ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ ሲያቀርቡ እንደገለፁት ባለፉት ወራት ሚሊዮኖችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በማንቀሳቀስ በቢሊዮን የሚገመት ሀብት በማሰባሰብ ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

የዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እያስተባበሩት ከግንቦት 18 ጀምሮ በተለያዩ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን በቤት እድሳት፣ በልዩ ድጋፍ ፣ በአረንጓዴ አሻራ ፣ በአካባቢ ፅዳት ፣ በጤና ተቋማት ነፃ አገልግሎት በመስጠት ፣ በማስተማር ፣ በሰላም ፣ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በማዋል ፣ የህይወት ልምዴን አካፍላለሁ በሚሉና በሌሎችም 15 ፕሮግራሞች የህዝባችንን የመረዳዳት እሴት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.