የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በአምስት ዙሮች እስከ ወረዳ ላሉ የመዋቅሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ
በአምስት ዙሮች ቢሮው በጋዘጤኝነትና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የካበተ ልምድ ያለቸውን ባለሙያዎች በመጠቀም ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ፤የከተማዋን ነዋሪዎች የመንግስት ሚዛናዊ መረጃ የማግኘት ፍላጎት ወቅቱን በጠበቀ አግባብ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ሙያዊ ስነ ዘዴዎች ላይ ማዕከል ያደረገ ነው።
በተከታታይ እስከ ታችኛው የቢሮው መዋቅር ድረስ እንዲሰጥ በተደረገው የዘርፉ የባለሙያዎችና አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ የሁሉም ወረዳ አስተዳደር መዋቅር ባለሙያዎች ፣ቡድን መሪዎችና የጽ/ቤት ኃላፊዎች ፤የየክፍለ ከተሞች የኮሙኒኬሽን ዘርፍ የቡድን መሪዎችን ጨምሮ የ52ም ሴክተር መስሪያ ቤቶች የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሮች በስልጠናው መረሀ-ግብር ላይ በመሳተፍ ሚዛናዊ የመንግስት መረጃ አያያዝና ስርጭትን አስመልክቶ መልካም ተሞክሮና ልምድ እንዲወስዱ ተደርጓል ።
የመንግስትን አጠቃላይ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በሚያሳይ መልኩ ከተማዋን በመልዕክትና አጀንዳ መምራት እንደሚገባ በስልጠናው መርሀ ግብር ማጠቃለያ ላይ ያሳሰቡት የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ፤ቅንጅታዊ አሰራርን በይበልጥ ማጠናከር ከሁሉም እንደሚጠበቅ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የከተማችንን ነዋሪዎች ሚዛናዊ የመንግሥት መረጃ ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ወቅቱን የጠበቀ የመረጃ ስርጭትና ተደራሽነት መርህን በጥብቅ መከተል እንደሚገባም በአንክሮ ያመላከቱት የቢሮ ኃላፊዋ፤ የጋዜጠኝነት ሙያ ዓለም አቀፍ የመረጃ አያያዝና ስርጭት መርህን ከእኛ አገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መልኩ ተግባራዊ ማድረግ ከሁላችንም የሚጠበቅ ተቋማዊ ኃላፊነተ ነውም ብለዋል ፡፡
የከተማዋን ሁለተናዊ ገፅታ ከማሻሻል ረገድ ብሎም ለህዝብ የሚያበረክቱት የላቀ ፋይዳ በጥናት ተለይቶ በከተማዋ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የልማት ስራዎችን በሚመለከት ወቅቱን የጠበቀ ተከታታይ መረጃ ለህዝብ የማድረስ ሙያዊ ኃላፊነትን በተዋረድ መወጣት የቢሮው መዋቅር አባላት የዘውትር ተግባር ልሆን እንደሚገባም ኃላፊዋ አክለው አመላክተዋል ፡፡
የስልጠና ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ፤ከወትሮዉ በተለየ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የከተማ አስተዳደሩን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለነዋሪዉ ለማሳወቅ ዝግጁ መሆናቸዉን ይፋ አድርገዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.