በዛሬው ዕለት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚገነባ ህንፃ የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጣቸው ገለፁ ፡፡
ዛሬ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ጋር በመሆን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱ ቤቶች ምትክ በቤተክርስቲያኒቱ የሚገነባ ህንፃ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠናል።
ቤተ ክህነት የከተማውን ልማት ሥራ በላቀ ሁኔታ በመደገፍ እና ለኮሪደር ልማት ስራዎች መጀመር፤ በማፍረስ ሂደትም ሆነ መልሶ በመገንባት ሂደት እንዲሁም ህንፃዎችን በማደስ ላደረገችው ተሳትፎ እና ተግባራዊ የሆነ ምላሽ ከልቤ ለማመስገን እወዳለሁ።
በዚህ አጋጣሚ ከቤተክርስቲያንቱ ለቀረበልኝ ምስጋናም እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.