ቃል በተግባር ! ከሁሉም በፊት የረዳን ፈጣሪን እናመሰግናለን !
በተያዘላቸው የሶስት ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቁትን ፒያሳ የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ እና የአራት ኪሎ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ገምግመናል።
አዲስ አበባን ከከተማው ነዋሪ ስንረከባት ልናስውባት፣ ልናለማት ቃል ገብተን ነው የጀመርነው። ለትውልድ የምትተርፍ፣ ቆሻሻ እና ስንፍና የሌለባት ከተማ ልናድርጋት ቃል ገብተን ነበር። እነሆ ቃላችንን ጠብቀናል !!
እንካችሁ የፀዳች አራዳን፤ እንካችሁ 24 / 7 የምትተጋ አራት ኪሎን፤ አሁን ለናንተ ምቹ አድርገናታል። ከውበቷና ከፅዳቷ ሳትጎድል ለትውልድ አኑሯት።
የኮሪደር ልማት ስራዎች ስንጀምር አብራችሁን ለተነሳችሁ፣ ለተባበራችሁ፣ ላሳመራችሁ ባለቤቶች፣ ለተባበራችሁ ባለ ሀብቶች፣ ተቋራጮች፣ በሙያችሁ ለተጋችሁ ሰራተኞች እና አመራሮች እንዲሁም የፌደራል ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ከሁሉ በላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለነበራቸው ድጋፍና ክትትል ምስጋናዬ ትልቅ ነው።
በአጠቃላይም ትናንት ምሽት ስንጎበኝ በጎዳናዎች ላይ ስራዎቹን እያደነቃችሁ ፍቅራችሁን ለገለፃችሁልን ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
ያስቀመጥንላችሁ ፎቶዎች ከፊል ገፅታዎች ናቸው። ሙሉውን ገፅታ መጥታችሁ ትመለከቱ ዘንድ እጋብዛችኋለሁ ።
ቀሪ የኮሪደር ስራዎቻችንን ፍጥነትን እና የፈጠራ መርህን ተከትለን አጠናቅቀን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን።
ጥራትን ማስጠበቅ እና ለዜጎቻችን ሁሉ የተመቸ ከባቢን መፍጠር ቅድሚያ የምንሰጣቸው ተግባራት ናቸው።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.