በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግማሽ ዓመቱ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግማሽ ዓመቱ የተሰሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ተደረጉ፤

በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት ፕሮጀክቶች በ60 ቀናት በልዩ ትኩረትና ክትትል የተሰሩ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ የመስሪያ ቦታ ሼዶች፣ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት G+2 ህንፃ፣ የመንገድ ፓርክ ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት G+4 ህንፃ እና በተለያዩ ወረዳዎች የተሰሩ ሌሎች በጥቅሉ 20 ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።

የክ/ከተማው ማና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ ባስተላለፉት መልዕክት የተመረቁት ፕሮጀክቶች ለማህበረሰቡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ጠቁመው ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜ እንዲጥናቀቁ ድጋፍና ክትትል ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ዛሬ የተመረቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት ፕሮጀክቶች ከተማ አስተዳደሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮክቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ተደራሽነትን ለማስፋት የያዘውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለው ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.