በፊንላንድ የዉጭ ንግድና ልማት ጉዳይ ሚኒስቴር የተመራዉ የልዑካን ቡድን የዓድዋ ሙዚየምን ጎበኙ።
የፊንላንድ የዉጭ ንግድና ልማት ሚኒስቴር ቪሌ ታቭዮ የዓድዋ ሙዚየም በጎበኙ ወቅት እንደተናገሩት የኢትዮጱያ ጀግኖች የሀገራቸውን ነጻነት ያረጋገጡ እና ለሌሎች ሃገራት ምሳሌ መሆን የቻለች ሀገር እንድትሆን አድርገዋል ብለዋል።
ይህ ጉብኝት በፊንላንድና በኢትዪጵያ ያለዉን የሁለትዮዎሽ ግንኙነት እና ተያያዥ ቀጠናዊ ጉዳዮች ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለዉም በኢትዮጵያ በኢኮኖሚዉ ዘርፍ የተሰማሩ በርካታ የፊንላንድ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት መገኘታቸዉን ገልፀዉ እነዚህን ተቋማት በኢትዮጵያ እንዲጠናከሩ ማድረግና ቀጠናዊ ትስስሩን በአፍሪካ ብሎም በአዉሮፓ ማስፋፋት እንደሚገባ አሳዉቀዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ መደሰታቸዉንና ትምህርት መዉሰዳቸዉን ገልፀዉ ለጉብኝቱ መሳካት ትብብር ለአደረጉላቸዉ ለከተማ አስተዳደሩንና ለተባባሪ አካላት በመንግስታቸዉና በልዑካኑ ስም ምስጋና ይገባል ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.