የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ አመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በ3 ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ መክሮ ውሳኔ አሳልፏል።
1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ባሉ የሴት ባክ (setback) ፕላን ትግበራ ከመንገድ ያላቸው ርቀት መጠን በካቢኔ ወስኖ ወደ ትግበራ መግባቱ ይታወሳል ።ከዚህ በፊት የተወሰኑ የሴት ባክ ለማስተግበር፤ ሂደቱን ለማሳለጥ እና አገልግሎቱን ለማፍጠን የቀረቡ በደንብ የተደገፉ ማብራሪያዎችን በጥልቀት ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
2. የመንገድ ዳር መብራት እና መሠረተ ልማቶች ለማስተዳደር የሚችል አስተዳደር ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን በዚህም የመንገድ ዳር መብራቶች እና መሠረተ ልማቶች ስንታንዳርዶችን ማውጣት፣ መቆጣጠር እንደ አስፈላጊነቱም በሚወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።
3. ደረጃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አደረጃጀት አሰራር ማሻሻያ ደንብን ካቢኔው መክሮበት አፅድቋል ። በይዘቱም ከተማዋ ከጊዜው ጋር የሚመጥን የፅዳት አጠባበቅ አጠቃቀም እና የቆሻሻ አወጋገድ እና የተሸከርካሪ የመንገድ አጠቃቀም እንዲሁም የመንገድ ፍሳሽ አወጋገድ አለአግባብ የመንገድ ላይ የመፀዳዳት ተግባራትን እንዲጠበቁ የሚያደርጉ የህግ ማዕቀፎች እና ተጥሰው ሲገኙ ለማስከበር ህገ ወጥ አሰራሮችን ለመቅጣት የሚያግዙ የህግ ማዕቀፎችን የያዘ ነዉ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.