የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥበቅ የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ እንዳይደረግ ክትትል ቁጥጥር እንደሚያደርግም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አሳወቋል።
በሀገራችን ውስጥ ያለውን ፍትሀዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤት ኪራይ ስርአቱ በህግ የሚመራ እና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ ሰለታመነበት የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መጋቢት 24/2016 መውጣቱ ይታወቃል።
የከተማ አስተዳደሩም የአዋጁም ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ተግባራዊ አርጓል።
ቢሆነም አዋጁ ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነበት ቀን ማለትም ከመጋቢት 24/2016 ጀምሮ መንግስት ከሚያስቀምጠው የኪራይ ውሳኔ ውጪ በአከራዮች የሚደረግ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ፈፅሞ የተከለከለ በመሆኑ አዋጁ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥበቅ የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
ይህ እንዳይፈፀምም ቢሮው ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚያደርግ እና የህግ ክልከላውን ተላልፎ የተገኙ አከራዮች ላይ በመመሪያ ቁጥር 7/2016 አንቀፅ 22 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አሳስቧል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.