የሴቶች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መርሃ ግብር “በጎ ፍቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ” በሚል መርሀ ግብር ተጀመረ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መርሃ ግብር “በጎ ፍቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ” በሚል መርህ አስጀምሯል።
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተዉ ባስተላለፉት መልእክት እንደተናገሩት በጎ ፈቃደኝት ለማህበረሰብ ለዉጥ ጉልህ ሚና ያለዉ መሆኑን ጠቅሰዉ በፈቃደኝነት የምናከናዉናቸዉ በጎ ስራዎች የጋራ ትብብርን የሚጠይቁ እና በፍላጎት የምንሰራቸዉ መሆኑን ሁላችንም አዉቀን ለተግባሩ ልንረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
አቶ አለማየሁ እጅጉ አክለዉም በዚህ የንቅናቄ መርሃ ግብር ሊደገፉ የሚገባቸዉን የማህበረሰብ ክፍሎች በጥንቃቄ ለይተን በመደገፍ ዉጤታማ ስራ በመስራት በከተማችን አምራች ዜጋን መፍጠር ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን በበኩላቸዉ እንደተናገሩት ቢሮው ከ20 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ ከ10 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በመግለፅ ለዚህ ስኬት ሁላችንም ተቀናጅተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.