የአዲስ አበባ እህት ከተማ በሆነችው የቻይናዋ ቤጂንግ ከተማ ኮሚኒስት ፓርቲ ምክትል ዋና ጸሃፊ እና የቤጂንግ የአመራር ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት በሆኑት ሚስተር ሊ ዌይ ከተመራው የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይተናል።
በውይይታችን ሁለቱ እህትማማች ከተሞች በቀጣይ በትራንስፖርት፣ በቤቶች ግንባታ፣ በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ያለንን ትብብር እንዲሁም የባህልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶቻችንን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.