ዛሬ የባለፉት አመታት ጥረታችንን በማጤን የ201...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የባለፉት አመታት ጥረታችንን በማጤን የ2016ቱን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ቅድመ ጅማሮ መርሃ ግብር አካሂደናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አመታት በ2011 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጠነሰሰው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት በየአመቱ የችግኝ ተከላ ስራ ስታካሂድ ቆይታለች። ዛሬ የባለፉት አመታት ጥረታችንን በማጤን የ2016ቱን ዙር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ቅድመ ጅማሮ መርሃ ግብር አካሂደናል። 

በተካሄደውም የአረንጓዴ ዓሻራ ቅድመ መክፈቻ መርሃ ግብር ሁነት የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት ይፋ ሆኗል። በመቀጠልም የሀገራዊውን የአረንጓዴ አሻራ ይዘት እና የስራ ውጤት በሰዋዊ ተረክ የሚያቀርብ አለምአቀፍ ዘጋቢ ፊልም የምረቃ እይታ ተካሂዷል። 

ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ሪፖርት እንዳመለከተው የደን ሽፋናችን በ2011 ዓመተ ምህረት ከነበረበት 17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ብሏል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመርሃ ግብሩ ባደረጉት ንግግር ይህን የዕድገት ውጤት ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።

#PMOEthiopia


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.