“ቴክኒክና ሙያ ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ 14ኛውን የከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ሳምንት ዛሬ ከፍተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ትጉሃን እጆችን ከስራ በማገናኘት ረገድ የቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ተቋማት ክህሎት መር አቅጣጫ ተከትለው እንዲሰሩ አስተዳደራችን ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረጉ ፍትሃዊ የስራ ዕድል ከመፍጠር በተጨማሪ ምርታማነትን ማሳደግ ችለናል።
የቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ተቋማት ኢንተርፕራይዞቻችን እንዳይከስሙ፣ ይልቁኑ አባሎቻቸው በጠንካራ የስራ ባህልና ክህሎት እየታነጹ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ተኪ ምርት አምርተው ለገበያ በማቅረብ፣ የዋጋ ንረቱን በመግራትና የውጭ ምንዛሬ በማዳን ትርጉም ያለው አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
ተቋማቱ ከማሰልጠን ባሻገር ተስማሚና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎችን እየለዩ በማላመድና በማሰልጠን ላይ የሚገኙ ሲሆን በተቋሞቻቸው የተገኙ ውጤቶችንም በዓውደ ርዕዩ ላይ የሚያቀርቡ ይሆናል።
የከተማችን ነዋሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለ6 ቀናት የሚቆየውን ዓውደ ርዕይ እንዲጎበኙ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ክህሎት መር የቴክኒክና ሞያ ስልጠና ለምርታማነትና ለፍትሀዊ የስራ ዕድል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.